በሀረር እና በሀረሪ ልጆች ቀልድ የለም (አፈንዲ ሙተቂ)

27/07/2021

በሀረር እና በሀረሪ ልጆች ቀልድ የለም (አፈንዲ ሙተቂ)
በሀረር እና በሀረሪ ልጆች ቀልድ የለም

በዚህ የረመዳን ወር ፖለቲካ አልጽፍም ብዬ ነበር። ይሁንና የምርጫ ቦርድ ተብዬው በሀረሪዎች ላይ የሚፈጽመው ግፍ ዝም የሚያስብል አልሆነም።

ቦርዱ በትናንትናው ዕለት "ሀገሪቱ ካሏት የምርጫ ጣቢያዎች መካከል እስከ አሁን ድረስ ምዝገባ እየተካሄደ ያለው በግማሽ ያህሉ ብቻ ነው" እያለ ሲያለቃቅስ ነበር። ከ25,000 በሚልቁት የምርጫ ጣቢያዎች ምዝገባ ሳይካሄድ ነው "ምርጫውን እናስፈጽማለን" የሚሉት።

ታዲያ ምዝገባውን ማካሄድ የቸገረው ምርጫ ቦርድ በሀረሪዎች ላይ የሚፈጽመውን ደባ ማስፈጸም ግን አላቃተውም። በሽግግሩ ዘመንም ሆነ በኢፌዴሪ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት እውቅና ተሰጥቶት ሲሰራበት የነበረውን የክልሉን የሁለት ምክር ቤቶች አሰራር በመሻር ክልሉን ኢዜማና ባልደራስ በተባሉ ወፍ-ዘራሽና ስግብግብ ፓርቲዎች ቁጥጥር ስር ለማስገባት የሚያደርገውን ደባ በትጋት ቀጥሎበታል።

ምርጫ ቦርድ የሀረሪዎችን መብት ለመቀማት ሲል "የአናሳ ህዝብን መብት መጠበቅ የሚል ህግ በእኛ አሰራር የለም፣ ሁሉም እኩል ተወዳድሮ ያሸንፋል" የሚል አነጋገር ይጠቅሳል። በዚህ አባባል መሠረት የሀረሪ ህዝብ የራሱን መሪዎች እንዳይመርጥ፣ በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ውስጥ አንድም ተወካይ እንዳይኖረው፣ በፌዴሬሽን ምክር ቤት ውስጥም ተወካይ እንዳይኖረው፣ ጉዳዩንም ሌሎች እንዲወስኑለት ይደረጋል ማለት ነው። የሚገርመው ነገር ከሀረር ጋር አንድም ታሪካዊ ቁርኝት የሌለውንና በወረራ እና በፍለሳ እየመጣ ከተማውን የሞላውን መደዴና ወንበዴ ለማስደሰት ሲባል ከሀረር ከተማ ጋር የብዙ ሺህ ዓመት ታሪካዊ ቁርኝት ያለው የነባሩ (native) ህዝብ መብትና ነፃነት ይደፍጠጥ መባሉ ነው።

የሆነው ይሁንና ምርጫ ቦርድ ይህንን ሸፍጥና ብልግና የሚሰራው በራሱ ተነሳሽነት ነው? በጭራሽ! ነገሩ ያለው በብልጽግና ጭንቅላት ውስጥ ነው። ይህ ፓርቲ የተገዥነት መንፈስ በተጠናወታቸው ገፍቲዎች የተሞላ ነው። የፓርቲው መሪ የሆነው አብይና እና ሌሎች አባላቱ ሁሌ የሚመኙት እንደ ኢዜማ ሰዎች መሆንን ነው። ኢዜማ እና ብልጽግና ስማቸው ቢለያይም ዓላማቸው አሁን ያለውን የፌዴራል ስርዓት አፍርሶ የአሃዳዊያንን ስርዓት መመለስ ነው። በፕላናቸው መሠረት በቅድሚያ የሀረሪ ክልልን ያፈርሳሉ። በማስከተል ደግሞ ሌሎች ክልሎችን ያፈርሳሉ።

ምርጫ ቦርድ እና ብልጽግና "ሀረሪዎች አናሳ ናቸው፣ ክልላቸውን ብናፈርስ ምንም አያመጡም" በሚል እብሪት ሴራቸውን ጀምረዋል። ነገር ግን ከሀረር ጋር በታሪክ፣ በንግድ፣ በባህልና በእምነት የተቆራኙትና ከወራሪው የምኒልክ ጦር ጋር በጨለንቆ የተፋለሙት የኦሮሞ፣ የሶማሊ፣ የአርጎባ፣ እና የአፋር ህዝቦች የሀረር እና የሀረሪዎችን ጉዳይ እንደራሳቸው ጉዳይ እንደሚያዩት ሁሉም ሰው ማወቅ አለበት።

ሀረርን የነካ ሁሉ ድራሹ ይጥፋ!!

በሀረር እና በሀረሪ ልጆች ቀልድ የለም

አፈንዲ ሙተቂ

የዐቢይ መንግሥት ሁሉንም ክልሎች ነካክቶ ማፍረስ ሲያቅተው አሁን ደግሞ ሌላ ስትራቴጂ ቀይሶ ተነስቷል። ይህም በህዝብ ብዛቱ ከሁሉም የሚያንሰውን የሀረሪ ክልል በማፍረስ በኢዜማ እና በባልደራስ ቁጥጥር ስር ማዋል ነው። በማስከተልም ከዚህ ያገኘውን ልምድ ተጠቅሞ ሌሎች ክልሎችን ወደ ማፍረስ ይሸጋገራል ማለት ነው።

ትሰማለህ ሰውዬው!!

ለሀረሪዎች ክልል የሰጣቸው ወያኔ አይደለም። ሀረሪዎች ራሳቸው በኩሉብ-ሀኖላቶ ዘመን እስከ UN-Trustee ድረስ ሄደው የታገሉበት ጉዳይ ነው። እኛ ኦሮሞዎችም "ሀረሪዎች በምኒልክ ወረራ ማግሥት የተነጠቁት የሀረር አሚሬት የራስ ገዝ ግዛት ሆኖ ሊመልስላቸው ይገባል" ብለን ከወያኔ በፊት ጥያቄውን አቅርበናል። በ1984 ደግሞ ሁሉም የኦሮሞ ድርጅቶች (OLF, IFLO, OALF, OPDO እና ሌሎችም) የሀረሪ ክልል ቢመሠረት ፈቃደኞች መሆናቸውን ገልጸዋል። ሶማሊዎችና አፋሮችም ከእኛ ጋር ሆነው የሀረሪ ክልል እንዲመሠረት ጠይቀዋል። የሀረሪ ልጆችም የሰነድ እና የቅርስ ማስረጃዎቻቸውን አቅርበው ተሟግተዋል። ያንን ጥያቄ ለመመልስ ሲባል ነው የሀረሪ ክልል የተመሠረተው። በአጭሩ በጨለንቆ ጦርነት ማግስት የከሰመው የሀረር አሚሬት ነው በ1984 "የሀረሪ ህዝብ ክልል" ሆኖ እንደገና ብቅ ያለው።

ሀረሪዎች የሀረር ከተማ ጥንተ-ነባር ነዋሪዎች ናቸው። ይሁንና በየጊዜው ወደ ከተማዋ የሚመጣው ፍልሰተኛ (immigrant) ቁጥር ከፍተኛ በመሆኑ በሌሎች ህዝቦች በብዙ ተበልጠዋል። native የሆነው ህዝብ ከፍልሰተኛው በቁጥር የሚያንስ ከሆነ ደግሞ የጥንተ ነባሩን ህዝብ መብት ለመጠበቅ ሲባል የተለያዩ እርምጃዎች መወሰዳቸው የተለመደ ነው። በዚህ መሠረት የክልሉ ምክር ቤቶች አወቃቀር በሌላው ክልል ከሚታወቀው ለየት ያለ ሆኗል።

በብርቱካን ሚደቅሳ የሚመራው የምርጫ ቦርድ ግን "ከቡድን መብት በፊት የግለሰብ ነፃነት ቅድሚያ ይሰጠዋል" በሚለው ኢዜማ-ቀመስ እሳቤ በመመራት ክልሉ ሲሰራበት የነበረውን የምርጫ ስርዓትና የምክር ቤቶች አሰራር ለማፍረስ ተነስቷል። ዓላማውም ክልሉን ኢዜማ እና ባልደራስ በሚባሉት የቦዞኔ ፖርቲዎች ቁጥጥር ስር ማስገባት ነው።

እኛ በዚህ ጊዜ ለመብታችን እየጮኽን ነው። የአናሳ ህዝቦች መብት በአጼዎቹ ስርዓት ናፋቂዎች ሲደፈጠጥ ደግሞ ለራሳችን ብቻ ሳይሆን ለሌሎች ጭቁን ህዝቦችም እንጮኻለን።

እንዲያውም አንድ ነገር አስታወስኩ

የዐብይ መንግሥት፣ የምርጫ ቦርድ፣ ኢዜማ፣ ጂንኒ ጀቡቲ አሁን ሞታቸውን ሊያፋጥኑ የፈለጉ ይመስለኛል። ሀረሪዎች ሲነኩ በአሚር ኑር እና በአው አባዲር መስጂድ ተሰብስበው የነካቸውን ሰው እንዲበቀልላቸው አላህን ይማጸናሉ። የሰሞኑ የባለጊዜዎች ቅብጠት የት እንደሚደርስም አብረን የምናየው ይሆናል።

Back to News Page

About Us

Australian Saay Harari Association is a non profit, ethnically based, social organization based in Melbourne, Australia.

Our Contacts

61 Elm Park Dr, Hoppers Crossing
Victoria 3029, Australia

(+614) 018 06 589
(+614) 1364 1816